የስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ የ2018 በጀት አመት የእስካሁኑን አፈጻጸም ከአጠቃላይ ባለሙያዎች ጋር ገመገመ።

ወራቤ/ መስከረም /2018 የስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ
የስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ የ2018 በጀት አመት የሁለት ወር አፈጻጸሙን ከሴክተሩ አጠቃላይ ባለሙያዎች ጋር ገመገመ።
ለውይይቱ መነሻ ሪፖርት በመምሪያው ልማት ዕቅድ ከቀረበ በኃላ በተግባር አፈጻጸም ሂደቱ የታዩ ጥንካሬና ጉድለቶች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
መድረኩን የመሩት የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የመምሪያው ኃላፊ አቶ ሙበራ ከማል ለአ/አደሩ ተጠቃሚነት የተቋማዊ አሰራርን ማጠናከር ወሳኝነት እንዳለው አጽኖት ሰጥተው አንስተዋል ።
በሁሉም ዘርፎችና ጽ/ቤቶች የተጀመሩ መልካም ስራዎችን በአርሶ አደር እና በቀበሌ ደረጃ በማስፋፋት እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶችን የሁሉም የማድረግ ስራ መሠራት እንዳለበት በማጠቃለያቸው አንስተዋል።
በመጨረሻም የምርትና ምርታማነትን የሚያሻሽሉ ቴክኒዎሎጂዎችን በሙሉ ፓኬጅ እንዲጠቀም በማድረግ እና ሕብረተሰቡን የሚለውጡ የተጀመሩ አዳዲስ ኢኒሼቲቮችን ውጤታማ በማድረግ ረገድ የባለሙያዎች ሚና የጎላ መሆኑን አንስተዋል ።
በመድረኩም የዞኑ ም/አስተዳዳሪ እና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙበራ ከማል፣ የእርሻ ልማት ዘር ኃላፊ አቶ ሳዲቅ አህመዲን እና የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከድር ሁሴን እንዲሁም የመምሪያው አጠቃላይ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
(ስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ)

2 thoughts on “የስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ የ2018 በጀት አመት የእስካሁኑን አፈጻጸም ከአጠቃላይ ባለሙያዎች ጋር ገመገመ።”

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Get 30% off your first purchase

X
Scroll to Top