በስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ የተመራ ልዑክ በላንፉሮ ወረዳና በጦራ ከተማ አስተዳደር በስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይ የተሰሩ ውጤታማ ስራዎች ምልከታ አደረገ፡፡

ወራቤ፣ መስከረም 11/2018 ዓ.ም፡-ስልጤ ዞን ኮሙኒኬሽን

በስልጤ ዞን ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ በተዘጋጀው ዓመታዊ ሴክቶሪያል ጉባኤ ተሳታፊ ባለድርሻ አካላት በላንፉሮ ወረዳ ፣በጦራ ከተማ አስተዳደር በሞዴል ወጣት ኢንተርፕራይዞች የተከናወኑ ስራዎችን ምልከታ አድርገዋል፡፡

በምልከታቸው በላንፉሮ ወረዳ በሻንቃ ጡፋ ቀበሌ በቲማቲምና በሌሎችም በአትክልትና በሰብል ልማት የተደራጁ ሞዴል ኢንተርፕራይዞች ምልከታ ተደርጓል፡፡

በሌላ በኩል በጦራ ከተማ አስተዳደር አውድ የወተት ከብት እርባታና አዱካሌ አጃክስ የወጣቶች ኢንተርፕራይዞች የተሰሩ ውጤታማ ስራዎችን ተመልክተዋል፡፡

የመስክ ምልከታው ከግዜያዊ የስራ ዕድል ወደ ቋሚ የስራ ዕድል ላይ የተቀየሩና ከኢንተርፕራይዝ ወደ ኢንቨስትመንት በመሸጋገር ላይ የሚገኙ የሞዴል ኢንተርፕራይዞች ልምድ ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለማስፋት ዓላማ ያደረገ ነው ተብሏል፡፡

በጉብኝቱ ላይ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ፣የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ ወ/ሮ ነኢማ ሙኒር፣የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ ሙበራ ከማል ፣የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ምክትል ሀላፊና የከተማ ስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ኃላፊ ፣የዞኑ ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያዋና ኃላፊ አቶ አብዱራህማን ወርቅቾ ፣የላንፉሮ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሸምሴ ጉንዳ ፣የጦራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሁሴን ሱነሞ ፣ ጨምሮ ሌሎች የዞንና ወረዳ አመራርና ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Get 30% off your first purchase

X
Scroll to Top