በምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ በአቶ ከይሬ ሀቢብ የተመራው የወረዳው አመራር አካላት በምስራቅ ስልጢ ወረዳ በመገኘት በግብርናው ዘርፍ የተሰሩ ስራዎች ላይ የልምድ ልውውጥ አደረጉ!By dep / October 3, 2025 ወራቤ፣ መስከረም 14/2018 (ስልጤ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን)በምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ በአቶ ከይሬ ሀቢብ የተመራው የወረዳው አስተባባሪዎች ና አመራር አካላት በምስራቅ ስልጢ ወረዳ ሳዳ ጎራ ቀበሌ ላይ በግብርናው ዘርፍ የተሰሩ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው የመስክ ምልከታ በማድረግ የልምድ ልውውጥ አድርገዋል።በዕለቱም የምስራቅ ስልጢ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሎ ፋኔ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ምስራቅ ስልጢና ምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረደ ትልቅ ትስስር እንዳለው በመግለጽ ወረዳው የተቀናጀ የልማት ስራዎችን በመስራት አርሷደሩን በሁለተናዊ የግብርና ዘርፍ ተጠቃሚ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከይሬ ሀቢብ እንደገለጹት፦የሁለቱ ወረዳ ግንኙነት ና የልምድ ልውውጥ አስፈላጊ መሆኑን በመጥቀስ የመስክ ጉብኝቱ በወረዳው የተሰሩ ጠንካራ የግብርና ልማት ስራዎችን ና ምርጥ ተሞክሮዎችን ወስዶ ለማስፋፋት ያለመ እንደሆነ ተናግረዋል።በወረዳው ሰዳ ጎራ ቀበሌ በሞዴል አርሷደሮች ማሳ የተቀናጀ የግብርና ልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።በዕለቱም የምስራቅ ስልጢ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ ና የግብርና ልማት ጽ/ቤት ዋና ሀላፊ አቶ ጀማል ሀሰን እንዳሉት፦አርሷደሩን በተቀናጀ የግብርና ልማት ስራዎች ና በኢንሼቲቭ ተግባራት ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።በመስክ ጉብኝቱም ወቅት እንደተገለጸው፦ የአርሷደሩን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ና ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በመሸጋገር የብልጽግና ጉዞን እውን ማድረግ ይገባል ተብሏል።የልምድ ልውውጡም የሁለቲዮሽን የልማት ስራዎችን ለማፋጠን ና አርሷደሩን በዘላቂነት በግብርናው ዘርፍ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሆነም ተገልጿል።ምስራቅ አዘርነት በርበሬ ኮሙኒኬሽን