እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን! የስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ በክልል አንደኛ በመውጣት ተሸላሚ ሆነ!By dep / October 12, 2025 ወራቤ፣ ጥቅምት 2 /2018የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የ2017 አፈፃፀምና ማጠቃለያ ጉባኤ እና የ2018 የበጋ ወቅት ስራዎች የንቅናቄ መድረክ ተካሄዷል።የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ባዘጋጀው የ2017 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ጉባኤ የስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ በአጠቃላይ ተግባር አፈፃፀም በክልሉ ካሉ መዋቅሮች 1ኛ ደረጃ በመውጣት የሶላር ፓምፕ፣ የኮምፒዩተር፣ ፕሪንተር፣ የዋንጫ እና ሰርተፍኬት ተሸላሚ ሆኗል።በሌላም በኩል መምሪያው በፀደይ ልማት 2ኛ እና በቅድመ በልግ አፈፃፀም 2ኛ ደረጃን ያገኘ ሲሆን የሳንኩራ ወረዳ በግብርና ጎዳና አፈፃፀም ልዩ ተሸላሚ መሆን ችሏል።በተያያዘም መሊቅ የስልጤ ገ/ህ/ስራ ዩኒየን፤ የሳንኩራ ወረዳ የግብርና ጎዳና ኢኒሼቲቭን በማሳካት ፤ አቶት አግሮ ኢንዱስትሪ ፤ አብደላና ቤተሰቡ ኃ.የተወሰነ ማሕበር ፤ የሳንኩራ ወረዳ አስተዳዳሪ ወ/ሮ ተሚማ ሙዴ የግብርና ጎዳና ኢኒሼቲቭ በብቃት በመምራት እንዲሁም ከሞዴል አርሶ ኣደርች፦ አቶ አወል ሁሴን ከወራቤ ከ/አስ በከተማ ግብርና፣ አቶ ጌቱ ሽፈራው ከወራቤ ከ/አስ በዓሳ ልማት፣ ወሮ ፈዲላ ከማል ከአ/ውሪሮ ወረዳ በተቀናጀ ግብርና፣ አቶ ሀምዛ አልዬ ከሁልባራግ ወረዳ ከተረጂነት ቀድሞ ለመላቀቅ ባደረጉት ጥረት የዋንጫ፣ ሰርተፍኬትና የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች ተበርክቶላቸዋል።ለዚህ ውጤት መገኘት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከታችሁ በየደረጃው የምትገኙ አመራሮችና ሠራተኞች፣ የመምሪችን አመራሮችና ባለሙያዎች ከፍተኛ ምስጋና እናቀርባለን ።የስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ በከፍተኛ አፈጻጸም አንደኛ ደረጃ በመያዝ የዋንጫ እንዲሁም የሶላር ፓምፕን ጨምሮ በአይነት ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ሽልማት ተበርክቶለታል።