በግብርናው ዘርፍ የተመዘገቡ መልካም ተሞክሮዎችን ወደ ሁሉም አካባቢዎች በማስፋት መዋቅሮችን የማቀራረብ ስራ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ አቶ ሙበራ ከማል ገለጹ።

ወራቤ፣ህዳር 4/2018 ስልጤ ኤፍ ኤም 92.6
የስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ ከዘርፎችና ጽ/ቤቶች የተወጣጣ የSMS(subject matter specialist) የባለሙያ ቡድን ድጋፍ ክትትል ግብረ መልስ ገመገመ።
የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙበራ ከማል መድረኩን የመሩት ሲሆን በሁሉም ዘርፎች የሚገኙ ወቅታዊ ተግባራትና አዳዲስ ኢኒሼቲቮች ዙሪያ የተደረገ ድጋፍ ክትትልን መነሻ ያደረገ ግብረ መልስ ከSMS ቲሙ ቀርቦ ወይይት ተደርጎበታል።
በመድረኩም የመምሪያው ኃላፊ አቶ ሙበራ ከማል በድጋፍ ክትትሉ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን የሁሉም ቀበሌና አርሶ አደሮች ማድረግ እንደሚገባና የታዩ ውስንነቶችን በአጭር ጊዜ ለመፍታት የሚያስችል ልዩ ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባር መግባት እንደሚገባ አሳስበዋል።
በውይይቱም የጽ/ቤትና ዘርፍ አመራሮች እና በSMS ድጋፉ የተሳተፉ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
መረጃው የስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ ነው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Get 30% off your first purchase

X
Scroll to Top